በዚያም ጊዜ እንዲህ ይሆናል፤ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት ከእንግዲህ ወዲህ በአቈሰሉአቸው ላይ አይደገፉም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።
2 ዜና መዋዕል 28:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ጊዜ ንጉሡ አካዝ ርዳታ ፈልጎ ወደ አሦር ንጉሥ ላከ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ንጉሡ አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ልኮ ርዳታ ጠየቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ንጉሡ አካዝ እርዳታ ፈልጎ ወደ አሦር ንጉሥ ላከ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤዶማውያን የይሁዳን ግዛት እንደገና በመውረር ብዙ ሰዎችን ማርከው ወሰዱ፤ ስለዚህ ንጉሥ አካዝ ርዳታ እንዲልክለት የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ንጉሡ አካዝ እርዳታ ፈልጎ ወደ አሦር ንጉሥ ላከ፤ |
በዚያም ጊዜ እንዲህ ይሆናል፤ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት የዳኑት ከእንግዲህ ወዲህ በአቈሰሉአቸው ላይ አይደገፉም፤ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።
እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።”
አሁንስ የግዮንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብፅ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወንዞችንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ?
ኤፍሬምም ደዌውን አያት፤ ይሁዳም ሥቃዩን አያት፤ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈውሳችሁ ዘንድ አልቻለም፤ ከእናንተም ሕማም አልተወገደም።