La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 25:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የአ​ሜ​ስ​ያስ ነገ​ሮች፥ እነሆ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአሜስያስ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የተከናወነው ሌላው ተግባር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የቀረውም የፊተኛውና የኋላኛው የአሜስያስ ነገር፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሜስያስ በዘመነ መንግሥቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የቀረውም የፊተኛውና የኋላኛው የአሜስያስ ነገር፥ እነሆ፥ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 25:26
12 Referencias Cruzadas  

የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም የሮ​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም ያደ​ረ​ገው የዮ​አስ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር እንደ ተዋጋ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የን​ጉ​ሡም የዳ​ዊት የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባ​ለ​ራ​እዩ በሳ​ሙ​ኤል ታሪክ፥ በነ​ቢ​ዩም በና​ታን ታሪክ፥ በባለ ራእ​ዩም በጋድ ታሪክ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገ​ሮች፥ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ሥ​ታት ታሪክ በጻ​ፈው በአ​ናኒ ልጅ በነ​ቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽ​ፈ​ዋል።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ከኢ​ዮ​አስ ሞት በኋላ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ።


አሜ​ስ​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል በራቀ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ ወደ ለኪ​ሶም ኮበ​ለለ፤ በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።


የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የዖ​ዝ​ያን ነገ​ሮች በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


የቀ​ሩ​ትም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገ​ሮች፥ ሰል​ፉም ሁሉ፥ ሥራ​ውም፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም የቀ​ሩት ነገ​ሮች፥ ቸር​ነ​ቱም፥ እነሆ፥ በአ​ሞጽ ልጅ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ ራእይ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛ​ውም ነገሩ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


የቀ​ሩ​ትም የኢ​ዮ​አ​ቄም ነገ​ሮች፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ርኵ​ሰት፥ በእ​ር​ሱም የተ​ገ​ኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል፤ ኢዮ​አ​ቄ​ምም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ ከአ​ባ​ቶ​ቹም ጋር በጋ​ኖ​ዛን ከተማ ተቀ​በረ። ልጁም ኢኮ​ን​ያን ከእ​ርሱ ቀጥሎ ነገሠ።