ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ አሽክት ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ስለ ተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር።
2 ዜና መዋዕል 25:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ እንዲህ ሲል ላከ፥ “የሊባኖስ ኵርንችት ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው” ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም ዱር አውሬዎች መጥተው ኵርንችቱን ረገጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ግን ለይሁዳ ንጉሥ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “አንድ የሊባኖስ ኵርንችት፣ ለአንድ የሊባኖስ ዝግባ፣ ‘ሴት ልጅህን ለልጄ ሚስት እንድትሆነው ስጠው’ አለው፤ ከዚያም አንድ የሊባኖስ ዱር አውሬ መጥቶ ኵርንችቱን በእግሩ ረገጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮስያስ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ እንዲህ ብሎ ላከ፦ “የሊባኖስ ኩርንችት፦ ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው’ ብሎ ወድ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኩርንችቱን ረገጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት ወደ ሊባኖስ ዛፍ መልእክት ልካ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል ጠየቀችው፤ ነገር ግን አንድ አውሬ በዚያ በኩል ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአያስ “የሊባኖስ ኵርንችት ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው’ ብሎ ወድ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ። |
ስለ ዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው እስከ አሽክት ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ስለ ወፎች ስለ ተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር።
የእግዚአብሔርም መልአክ ለሙሴ በእሳት ነበልባል በቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም፥ ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ፥ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።