La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 25:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሜ​ስ​ያ​ስም የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች ከገ​ደለ በኋላ የሴ​ይ​ርን ልጆች አማ​ል​ክት አመጣ፤ የእ​ር​ሱም አማ​ል​ክት ይሆኑ ዘንድ አቆ​ማ​ቸው፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውና ይሠ​ዋ​ላ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሜስያስም ኤዶማያውያንን ደምስሶ በተመለሰ ጊዜ፣ የሴይርን ሕዝብ አማልክት ይዞ መጣ፤ ለራሱም አማልክት አድርጎ በማቆም ሰገደላቸው፤ መሥዋዕትም አቀረበላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሜስያስም የኤዶማውያንን ሰዎች ከገደለ በኋላ የሴይርን ልጆች አማልክት አመጣ፥ የእርሱም አማልክት እንዲሆኑ አቆማቸው፥ ይሰግድላቸውም ያጥንላቸውም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሜስያስ ኤዶማውያንን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ይዞ መጣ፤ አማልክት አድርጎም በማቆም ሰገደላቸው፤ ዕጣንም አጠነላቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሜስያስም የኤዶማያስን ሰዎች ከገደለ በኋላ የሴይርን ልጆች አማልክት አመጣ፤ የእርሱም አማልክት ይሆኑ ዘንድ አቆማቸው፤ ይሰግድላቸው፥ ያጥንላቸውም ነበር።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 25:14
12 Referencias Cruzadas  

ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወሰ​ዱ​አ​ቸው።


በዚ​ያን ጊዜም አሜ​ስ​ያስ፥ “ና እርስ በር​ሳ​ችን ፊት ለፊት እን​ተ​ያይ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮ​አ​ካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


አሜ​ስ​ያስ ግን ከእ​ርሱ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ዳ​ይ​ሄዱ ያሰ​ና​በ​ታ​ቸው ጭፍ​ሮ​ችም ከሰ​ማ​ርያ ጀም​ረው እስከ ቤት​ሮን ድረስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ላይ አደጋ ጣሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሦስት ሺህ ገደሉ፤ ብዙም ምርኮ ማረኩ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልብ አይ​ደ​ለም።


ንጉ​ሡም፥ “የመ​ቱ​ኝን የደ​ማ​ስ​ቆን አማ​ል​ክት እፈ​ል​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የሶ​ር​ያን ንጉሥ እር​ሱን ረድ​ተ​ው​ታ​ልና እኔ​ንም ይረ​ዱኝ ዘንድ እሠ​ዋ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለ። ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዕን​ቅ​ፋት ሆኑ።


ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው አት​ስ​ገድ፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም አት​ሥራ፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ አፍ​ር​ሳ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብ​ራ​ቸው።


ለሰ​ውም ማገዶ ይሆ​ናል፤ ከእ​ር​ሱም ወስዶ ይሞ​ቃል፤ አን​ድ​ዶም እን​ጀራ ይጋ​ግ​ር​በ​ታል፤ ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን ጣዖ​ታ​ትን አበ​ጅቶ ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።


ማንም በልቡ አያ​ስ​ብም፥ “ግማ​ሽ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ያ​ለሁ፤ በፍ​ም​ዋም ላይ እን​ጀ​ራን ጋግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በል​ቻ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም አስ​ጸ​ያፊ ነገር አደ​ር​ጋ​ለ​ሁን? ለዛ​ፍስ ግንድ እሰ​ግ​ዳ​ለ​ሁን? እን​ዲ​ልም ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋል የለ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ከ​ተ​ሉት ከንቱ ነገር አስ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይ​ሁዳ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።


ነገር ግን እን​ዲህ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን አፍ​ርሱ፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰባ​ብሩ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቍረጡ፥ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስል በእ​ሳት አቃ​ጥሉ።