ዘንበሪም ከዚያች ተራራ ባለቤት ከሴሜር በሁለት መክሊት ብር የሳምሮንን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠራትንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራት።
2 ዜና መዋዕል 25:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜስያስ ግን ከእርሱ ጋር ወደ ሰልፍ እንዳይሄዱ ያሰናበታቸው ጭፍሮችም ከሰማርያ ጀምረው እስከ ቤትሮን ድረስ በይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጣሉ፤ ከእነርሱም ሦስት ሺህ ገደሉ፤ ብዙም ምርኮ ማረኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ አሜስያስ ያሰናበታቸውና በጦርነቱ እንዳይካፈሉ የከለከላቸው ወታደሮች፤ ከሰማርያ እስከ ቤትሖሮን ያሉትን የይሁዳ ከተሞች ወረሩ፤ ሦስት ሺሕ ሰው ገደሉ፤ እጅግ ብዙ ምርኮም ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሜስያስ ግን ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያሰናበታቸው ጭፍሮች ከሰማርያ ጀምረው እስከ ቤትሖሮን ድረስ በይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ከእነርሱም ሦስት ሺህ ሰዎች ገደሉ፥ ብዙ ምርኮም ማረኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ ወቅት፥ አሜስያስ ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዲሄዱ ያልፈቀደላቸው የእስራኤል ወታደሮች በሰማርያና በቤትሖሮን መካከል በሚገኙት በይሁዳ ከተማዎች ላይ አደጋ በመጣል ሦስት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፤ እጅግ የበዛ ምርኮም ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜስያስ ግን ከእርሱ ጋር ወደ ሰልፍ እንዳይሄዱ ያሰናበታቸው ጭፍሮች ከሰማርያ ጀምረው እስከ ቤትሖሮን ድረስ በይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጣሉ፤ ከእነርሱም ሦስት ሺህ ገደሉ፤ ብዙ ምርኮም ማረኩ። |
ዘንበሪም ከዚያች ተራራ ባለቤት ከሴሜር በሁለት መክሊት ብር የሳምሮንን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠራትንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራት።
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮሳፍጥ በሁለተኛው ዓመት የዘንበሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ።
የይሁዳም ልጆች ደግሞ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ማረኩ። ወደ ዐለቱም ራስ ላይ አመጡአቸው፤ ከዐለቱም ራስ ላይ ጣሉአቸው፤ ሁሉም ተፈጠፈጡ።
አሜስያስም የኤዶምያስን ሰዎች ከገደለ በኋላ የሴይርን ልጆች አማልክት አመጣ፤ የእርሱም አማልክት ይሆኑ ዘንድ አቆማቸው፤ በፊታቸውም ይሰግድላቸውና ይሠዋላቸው ነበር።
ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ።