እነሆ፥ እግዚአብሔር ሕዝብህንና ልጆችህን፥ ሚስቶችህንም፥ ያለህንም ንብረት ሁሉ በታላቅ መቅሠፍት ይቀሥፋል።
2 ዜና መዋዕል 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትታመማለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም ራስህ በየዕለቱ እየባሰ በሚሄድ የአንጀት በሽታ ክፉኛ ትታመማለህ፤ በመጨረሻም ሕመሙ አንጀትህን ወደ ውጭ ያወጣዋል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪ ወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትያዛለህ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ በማይድን ክፉ የአንጀት በሽታ ትሠቃያለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትታመማለህ።” |
እነሆ፥ እግዚአብሔር ሕዝብህንና ልጆችህን፥ ሚስቶችህንም፥ ያለህንም ንብረት ሁሉ በታላቅ መቅሠፍት ይቀሥፋል።
ውኃውን ካጠጣት በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ራስዋን አርክሳና ባልዋን ቸል ብላው ከሆነ፤ የመርገሙ መራራ ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል፤ ሆድዋንም ይሰነጥቀዋል፤ ጎኗም ይረግፋል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።
ከዚህም በኋላ ይህ ሰው በዐመፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በምድር ላይም በግንባሩ ወደቀና ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።
እግዚአብሔር መቅሠፍትህን፥ የዘርህንም መቅሠፍት፥ ታላቅና የሚያስፈራ መቅሠፍትን፥ ለብዙ ጊዜ የሚኖር ክፉ ደዌና ሕማምን ሁሉ ያመጣብሃል።
ደግሞም ይህ ሕግ ባለበት መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፈውን ደዌ ሁሉ፥ መቅሠፍትንም ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር ያመጣብሃል።
ከፈራህበት ከልብህ ፍርሀት የተነሣ፥ በዐይንህም ካየኸው የተነሣ፥ ሲነጋ እንዴት ይመሽ ይሆን? ትላለህ፤ ሲመሽም እንዴት ይነጋ ይሆን? ትላለህ።