La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 20:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ተር​ሴ​ስም የሚ​ሄ​ዱ​ትን መር​ከ​ቦች ያሠራ ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ መር​ከ​ቦ​ቹ​ንም በጋ​ሲ​ዮ​ን​ጋ​ብር አሠሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦችን ለመሥራትም ተስማሙ፤ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር አሠሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮሣፍጥም ወደ ተርሴስ የሚሄዱትን መርከቦች ለመሥራት ከእርሱ ጋር ተባበረ፤ መርከቦቹንም በዔጽዩን-ጋብር አሠሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁለቱም በመተባበር ዔጽዮንጋብር ተብሎ በሚጠራ ወደብ ላይ ውቅያኖስን አቋርጠው ሊጓዙ የሚችሉ መርከቦችን ሠርተው ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ተርሴስም የሚሄዱትን መርከቦች ያሠሩ ዘንድ አንድ ሆኑ፤ መርከቦቹንም በዔጽዩንጋብር አሠሩ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 20:36
7 Referencias Cruzadas  

ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር በኤ​ላት አጠ​ገብ ባለ​ችው በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር መር​ከ​ቦ​ችን ሠራ።


የማ​ር​ሶስ ሰው የኢ​ያ​ድያ ልጅ አል​ዓ​ዛር፥ “ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​ብ​ረ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን አፍ​ር​ሶ​ታል” ብሎ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ላይ ትን​ቢት ተና​ገረ። መር​ከ​ቦ​ቹም ተሰ​በሩ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም ይሄዱ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


ሰሎ​ሞ​ንም የዚ​ያን ጊዜ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በባ​ሕር ዳር ወዳሉ ወደ ጋሴ​ዎ​ን​ጋ​ብ​ርና ወደ ኤላት ሄደ።


ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ተር​ሴስ የሚ​ሄዱ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በሦ​ስት በሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ ጊዜ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ወር​ቅና ብር፥ የዝ​ሆ​ንም ጥር​ስና ዝን​ጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር።


ከኤ​ብ​ሮ​ናም ተጕ​ዘው በጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤር ሰፈሩ።