እስራኤልም ከሴቄም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእስራኤልንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።
2 ዜና መዋዕል 20:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር ነገሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሀት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንዴት እንደ ተዋጋቸው በሰሙ መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ወደቀባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ የጌታር ፍርሃት አደረባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንዴት እንደ ተዋጋ የሰሙ መንግሥታት ሁሉ የእግዚአብሔር ፍርሀትና ድንጋጤ ዐደረባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሃት ሆነ። |
እስራኤልም ከሴቄም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእስራኤልንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።
እግዚአብሔርም ለሶርያውያን የሰረገላ ድምፅ፥ የፈረስ ድምፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰምቶአቸዋልና፥ እርስ በርሳቸው “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ይከቡን ዘንድ የኬጤዎናውያንንና የግብፃውያንን ነገሥት ቀጥሮ አምጥቶብናል” ይባባሉ ነበር።
አሳም፥ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌዶር ሀገር ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፤ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ ስለ ወደቀባቸው በጌዶር ዙሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ መቱ፤ በከተሞቹም ውስጥ እጅግ ብዙ ምርኮና ብዝበዛ ነበርና ከተሞቹን ሁሉ ማረኩ።
በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ የምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ፤ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም።
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፥ “እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።
በፊትህ መፈራትን እሰድዳለሁ፤ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ እንዲሸሹልህ አደርጋለሁ።
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የፊኒቃውያን ነገሥት ሁሉ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩ ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ አእምሮአቸውን ሳቱ።