La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 18:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንድ ሰውም ቀስ​ቱን በድ​ን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በጥ​ሩሩ መጋ​ጠ​ሚያ በኩል ሳን​ባ​ውን ወጋው። ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና እጅ​ህን ግታ፤ ከጦ​ር​ነት ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁን እንጂ አንዱ ቀስቱን በነሲብ ቢያስፈነጥረው፣ በጥሩሩ መጋጠሚያዎች መካከል ዐልፎ የእስራኤልን ንጉሥ ወጋው። ንጉሡም ሠረገላ ነጂውን “ተመለስና ከጦርነቱ አውጣኝ፤ ቈስያለሁና” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድ ሰውም ቀስቱን በድንገት ገትሮ የእስራኤልን ንጉሥ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል ሳንባውን ወጋው። ሰረጋለኛውንም፦ “ተወግቻለሁና ሠረገላውን አዙር ከጦርነቱም ውስጥ አውጣኝ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይሁን እንጂ አንድ የሶርያ ወታደር በአጋጣሚ ያስፈነጠረው ፍላጻ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል አልፎ አክዓብን መታው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን “እኔ ቈስያለሁ! ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ!” ሲል አዘዘው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንድ ሰውም ቀስቱን በድንገት ገትሮ የእስራኤልን ንጉሥ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል ሳንባውን ወጋው። ሰረጋለኛውንም “ተወግቻለሁና እጅህን ግታ፤ ከሰልፍም ውስጥ አውጣኝ” አለው።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 18:33
5 Referencias Cruzadas  

የተ​ጠ​ሩ​ትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም በየ​ዋ​ህ​ነት ሄዱ፤ ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ከቶ አያ​ው​ቁም ነበር።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም አለ​ቆች የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እን​ዳ​ል​ሆነ ባዩ ጊዜ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ።


በዚ​ያም ቀን ጦር​ነት በረታ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በሶ​ር​ያ​ው​ያን ፊት እስከ ማታ ድረስ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ራሱን ይደ​ግፍ ነበር፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ሞተ።


ቀስ​ተ​ኞ​ቹም ንጉ​ሡን ኢዮ​ስ​ያ​ስን ወጉት፤ ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እጅግ ቈስ​ያ​ለ​ሁና ከሰ​ልፉ ውስጥ አው​ጡኝ” አላ​ቸው።