ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ኤርያስ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበረ፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ተገኙ፤
1 ዜና መዋዕል 6:81 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንና መሰማሪያዋ፥ ኢያዜርና መሰማሪያዋ ተሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንና መሰማሪያዋ፥ ኢያዜርና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሴቦንና ያዕዜር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንና መሰምርያዋ፥ ኢያዜርና መሰማርያዋ ተሰጡ። |
ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ኤርያስ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበረ፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ተገኙ፤
“መንግሥታትንና አሕዛብን ዕድል ፈንታ አድርገህ ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
እስራኤልም እነዚህን ከተሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስራኤልም በአሞራውያን ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንና በመንደሮቹ ሁሉ ተቀመጠ።
ሙሴም ሰላዮቹን ወደ ኢያዜር ላከ፤ እርስዋንና መንደሮችዋንም ያዙ፤ በዚያም የነበሩትን አሞሬዎናውያንን አባረሩ።
ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር የከብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።
ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።