1 ዜና መዋዕል 6:76 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቄርያታይምና መሰማሪያዋ ተሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንፍታሌም ግዛት በገሊላ ምድር የምትገኘው ቄዴሽ፥ ሐሞንና ቂርያታይም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማርያዋ፥ ሐሞንና መሰማርያዋ፥ ቂርያታይምና መሰማርያዋ ተሰጡ። |
በንፍታሌም ባለው በተራራማው ሀገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው ሀገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው ሀገር ኬብሮን የምትባለውን የአርቦቅን ከተማ ለዩ።
ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማርያዋን፥ ኤማትንና መሰማርያዋን፥ ቃርቴንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤