1 ዜና መዋዕል 6:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ለማስተስረይ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንና ዘሮቹ የዕጣን መባና በመሠዊያው ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ ያቀርቡ ነበር፤ እንዲሁም በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የአምልኮ ሥርዓትና እግዚአብሔር የእስራኤልን ኃጢአት ለሚያስተሰርይበት መሥዋዕት ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ፤ እነርሱም ይህን ሁሉ የሚፈጽሙት እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለሙሴ በሰጠው መመሪያ መሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሠርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፤ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። |
ለመክበራቸው እጆቻቸውን ይቀድሱ ዘንድ በተቀደሱበት በዚያ ቦታ ይብሉት፤ የባዕድ ልጅ ግን አይብላው፤ የተቀደሰ ነውና።
በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
እንዲህም በወይፈኑ ያደርጋል፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት በታረደው ወይፈን እንደ አደረገ እንዲሁ በዚህ ያደርጋል፤ ካህኑም ኀጢአታቸውን ያስተሰርያል፤ ኀጢአቸውም ይሰረይላቸዋል።
ካህኑም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ያስተሰርይላቸዋል፤ ባለማወቅ ነበርና ይሰረይላቸዋል፤ እነርሱም ስለ ኀጢአታቸውና ስላለማወቃቸው ቍርባናቸውንና መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ።
እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦