1 ዜና መዋዕል 6:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በምስክሩ ድንኳን ማደሪያ ፊት በበገና እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ለአገልግሎታቸው ይቆሙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሰሎሞን የጌታን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ከመሥራቱ በፊት እግዚአብሔር በሚመለክበት ድንኳን የመዘመር ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፤ የሥራቸውንም ቅደም ተከተል በተዘጋጀላቸው ተራ መሠረት ይፈጽሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። |
ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን በየሰሞናቸው አገልጋዮችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረ።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡና ያገለግሉ ዘንድ፥ ያመሰግኑም፥ ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን መደበ።
የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳፍም፥ እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶትም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር።
በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈው በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕርጋቸው፥ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው አቆሙ።
ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ፤ እነሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ደቡብ ይመለከት ነበረ፤ ሌላውም ወደ ደቡብ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።