La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 29:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆቹ ለእግዚአብሔር ስላደረጉት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለጌታ በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ፍጹም ደስ ተሰኘ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቡ በፈቃዳቸውና በሙሉ ልብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፤ እጅግ ብዙ ሀብት ገቢ በመሆኑም ደስ አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም ከመጠን በላይ ደስ ተሰኘ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ በታላቅ ደስታ ደስ አለው።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 29:9
22 Referencias Cruzadas  

እንደ ዛሬው ቀን በሥ​ር​ዐቱ እን​ሄድ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እን​ጠ​ብቅ ዘንድ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ልባ​ችን ፍጹም ይሁን።”


እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ከሚ​ያ​መ​ጣው ካህ​ናቱ ለራ​ሳ​ቸው ይው​ሰዱ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ይጠ​ግ​ኑ​በት” አላ​ቸው።


ንጉሡ ዳዊ​ትም በጉ​ባ​ኤው ሁሉ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አባ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ቡሩክ ነህ።


አም​ላኬ ሆይ፥ ልብን እን​ደ​ም​ት​መ​ረ​ምር፥ ጽድ​ቅ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ድድ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም በልቤ ቅን​ነ​ትና በፈ​ቃዴ ይህን ሁሉ አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም በዚህ ያለው ሕዝ​ብህ በፈ​ቃዱ እን​ዳ​ቀ​ረ​በ​ልህ በደ​ስታ አይ​ቻ​ለሁ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል የዝ​ክሪ ልጅ ማስ​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።


አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ሰጡ፤ እስ​ኪ​ሞ​ላም ድረስ በሣ​ጥኑ ውስጥ አስ​ገ​ቡት።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም መጥ​ተው ክም​ሩን ባዩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ። ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባረኩ።


በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ ሁሉ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ካቀ​ረ​ቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወ​ርቅ፥ በገ​ን​ዘ​ቦ​ችና በእ​ን​ስ​ሶች፥ በሌ​ላም ስጦታ ይረ​ዷ​ቸው ነበር።


ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።


ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳ​ጆ​ቹ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ቹን ጠርቶ፦ የጠ​ፋ​ች​ኝን በጌን አግ​ኝ​ቼ​አ​ታ​ለ​ሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ ይላ​ቸ​ዋል።


ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስ​ታ​ች​ሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


እነ​ርሱ ሲቻ​ላ​ቸው፥ ሳይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም እን​ስጥ በማ​ለት ቈራ​ጦች ለመ​ሆ​ና​ቸው ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ።


በጌ​ታ​ችን እጅግ ደስ አለኝ፤ ቢሳ​ና​ችሁ እንኳ አሁ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡ​ልኝ፥ ከዱሮ ጀምሮ ለእኔ ችግር ታስቡ፥ ትተ​ጉም ነበ​ርና።


ልቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ታዘ​ዘው ትእ​ዛዝ ነው፤ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት።