1 ዜና መዋዕል 29:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቤት ግንቦች ይለበጡበት ዘንድ ከኦፌር ወርቅ ሦስት ሺህ መክሊት ወርቅ፥ ሰባት ሺህ መክሊትም ጥሩ ብር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሦስት ሺሕ መክሊት የኦፊር ወርቅና ሰባት ሺሕ መክሊት ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቶቹ ግንብ እንዲለብጡበት ከኦፊር ወርቅ ሦስት ሺህ መክሊት ወርቅ፥ ሰባት ሺህም መክሊት ጥሩ ብር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ መሠረት መቶ ሺህ ኪሎ የኦፊር ወርቅና ሁለት መቶ አርባ ሺህ ኪሎ የሚሆን ንጹሕ ብር የቤተ መቅደሱን ግንቦች ለማስጌጥና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤቶቹ ግንብ ይለበጡበት ዘንድ ከኦፊር ወርቅ ሦስት ሺህ መክሊት ወርቅ፥ ሰባት ሺህም መክሊት ጥሩ ብር፥ |
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።
ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቤት ስለ ወደድሁ፥ ለመቅደሱ ከሰበሰብሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና እነሆ፥ ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
በሠራተኞች እጅ ለሚሠራው ሥራ ሁሉ ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን ሰጥቻለሁ። ዛሬ በዚች ቀን በፈቃዱ አገልግሎቱን ለእግዚአብሔር የሚፈጽም ማን ነው?”
እያንዳንዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያንዳንዱም ድስት ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚህም ዕቃ ሁሉ ብር በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።