ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
1 ዜና መዋዕል 29:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን የእግዚአብሔርን ቤት ስለ ወደድሁ፥ ለመቅደሱ ከሰበሰብሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና እነሆ፥ ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነዚህ ካዘጋጀኋቸው ነገሮች ሁሉ በላይ እኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካለኝ ታላቅ ፍቅር የተነሣ ከራሴ ንብረት ብዙ ብርና ወርቅ ሰጥቼአለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ። |
ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
ንጉሡም ዳዊት ኦርናን፥ “አይደለም፥ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በተገቢው ዋጋ እገዛዋለሁ” አለው።
እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤት ወርቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረትን፥ እንጨትን፥ ደግሞም መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።