1 ዜና መዋዕል 27:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሳሮንም በሚሰማሩ ከብቶች ላይ ሳሮናዊው ሰጥራይ ሹም ነበረ፤ በሸለቆዎቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ የዓድላይ ልጅ ሳፋጥ ሹም ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰማሩት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ፤ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሳሮንም በሚሰማሩ ከብቶች ላይ ሳሮናዊው ሰጥራይ ሹም ነበረ፤ በሸለቆቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ ሹም ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሳሮንም በሚሰማሩ ከብቶች ላይ ሳሮናዊው ሰጥራይ ሹም ነበረ፤ በሸለቆቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ ሹም ነበረ፤ |
በምድረ በዳውም ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ በቆላውና በደጋው ብዙ እንስሶች ነበሩትና፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ገዛሁ፤ በቤት የተወለዱ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ነበሩኝ።
የዮርዳኖስም ምድረ በዳ ያብባል፤ ሐሤትንም ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብርና የቀርሜሎስ ክብር ይሰጠዋል፤ ሕዝቤም የጌታን ክብር፥ የአምላክንም ግርማ ያያሉ።
ተመልሳችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞራውያን ተራራ፥ ወደ አረባም ሀገሮች ሁሉ፥ በተራራውም፥ በሜዳውም፥ በሊባም፥ በባሕርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ሂዱ።
በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ።