በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዳኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ፤ በሜዳውም፥ በከተሞቹም፥ በመንደሮቹም፥ በግንቦቹም ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤
1 ዜና መዋዕል 27:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሬቱን በሚያበጃጁትና እርሻውን በሚያርሱት ላይ የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሬቱን በሚያበጃጁትና እርሻውን በሚያርሱት ላይ የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሬቱን በሚያበጃጁትና እርሻውን በሚያርሱት ላይ የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ፤ |
በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዳኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ፤ በሜዳውም፥ በከተሞቹም፥ በመንደሮቹም፥ በግንቦቹም ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤
በወይንም ቦታዎች ላይ ራማታዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወይንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚሆነው በወይኑ ሰብል ላይ የሳፍኒው ዘብዲ ሹም ነበረ።
በምድረ በዳውም ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጕድጓድም ማሰ፤ በቆላውና በደጋው ብዙ እንስሶች ነበሩትና፤ ደግሞም እርሻ ይወድድ ነበርና በተራራማውና በፍሬያማው ስፍራ አራሾችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።