1 ዜና መዋዕል 26:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኬብሮናውያን ሐሳብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ፥ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኬብሮናውያን፤ ለሐሻብያ፣ ጠንካራና ጐበዝ የሆኑ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሡም አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኬብሮናውያን ሐሸብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለጌታ ሥራ ሁሉ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኬብሮናውያን ወገን ሐሻብያና ወንድሞቹ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው በእስራኤል አገር ለመንፈሳዊ ሥራና ለመንግሥት አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኬብሮናውያን ሐሸብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሹመው ነበር። |
እነሆም፥ ለእግዚአብሔር በሚሆነው ነገር ሁሉ የካህናቱ አለቃ አማርያ፥ በንጉሡም ነገር ሁሉ የይሁዳ ቤት አለቃ የይስማኤል ልጅ ዝባድያስ በላያችሁ ተሾመዋል፤ ጸሐፍቱና ሌዋውያኑ ደግሞ በፊታችሁ አሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፤ እግዚአብሔር መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።
ለቀዓትም የእንበረም ወገን፥ የይስዓር ወገን፥ የኬብሮንም ወገን፥ የአዛሔልም ወገን ነበሩ፤ የቀዓት ወገኖች እነዚህ ናቸው።