1 ዜና መዋዕል 25:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹም ታላቁም፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ እነርሱም ፍጹማንና የተማሩ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ሁሉም በተመሳሳይ መልኩ፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ። |
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የንዋያተ ቅዱሳቱና የእግዚአብሔር ቤት አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
የመጀመሪያው ዕጣ ለአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ለወንድሞቹና ለልጆቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ ሁለተኛውም ዕጣ ለጎዶልያስ ለልጆቹና ለወንድሞቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤
እነሆም፥ ንጉሡ በመግቢያው በዓምዱ አጠገብ ሆኖ በንጉሡም ዙሪያ አለቆችና መለከተኞች፥ መኳንንትም ቆመው አየች። ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከቱን ይነፉ ነበር፤ መዘምራንም በዜማ ዕቃ እያዜሙ የምስጋና መዝሙር ይዘምሩ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።
የሌዋውያኑም አለቆች አሳብያ፥ ሰርብያ፥ ኢያሱ፥ የቀድምኤልም ልጆች፥ ወንድሞቻቸውም እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በእነርሱ ፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።