1 ዜና መዋዕል 24:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ በአባታቸው በአሮን እጅ እንደ ተሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየአገልግሎታቸው ቍጥራቸው ይህ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዓት ወደ ጌታ ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ሰዎች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የቀድሞ አባታቸውን አሮንን ባዘዘው መሠረት ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው የሥራ ድርሻቸው ክፍፍል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዐት ይህ ነበረ። |
እነሆ፥ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ከሦስት አንድ እጅ በመግቢያ በሮች በረኞች ሁኑ፤
ሌዋውያንና ይሁዳም ሁሉ ካህኑ ኢዮአዳ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ካህኑም ኢዮአዳ ሰሞነኞቹን አላሰናበተም ነበርና እያንዳንዱ ከሰንበት መጀመሪያ እስከ ሰንበት መጨረሻ ሰዎችን ወሰደ።
እንግዲህ ሕዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ወደ ፊት ስለምን ያስፈልጋል?