La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 23:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው ቆመው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገ​ንና ለማ​ክ​በር፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በየዕለቱም እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጧት ጧት ይቆሙ ነበር፤ ይህንም ማታ ማታ

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው ጌታን በማመስገንና በማክበር፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዘወትር ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ነገር በሚቃጠልበት በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻና በሌሎችም በዓላት እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር የእነርሱ ተግባር ነበር፤ በየጊዜው ይህን አገልግሎት የሚፈጽሙ ሌዋውያን ቊጥራቸው ምን ያኽል መሆን እንደሚገባው ደንቦች ነበሩ፤ ሌዋውያን እግዚአብሔርን ለማምለክ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ለሁልጊዜ ተመድበዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሥራቸውም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር፥

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 23:30
19 Referencias Cruzadas  

ደግ​ሞም ገጸ ኅብ​ስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በም​ጣ​ድም ቢጋ​ገር፥ ቢለ​ወ​ስም ለእ​ህል ቍር​ባን በሆ​ነው በመ​ል​ካሙ ዱቄት በመ​ስ​ፈ​ሪ​ያና በልክ ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም እንደ ሥር​ዐቱ ቍጥር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘወ​ትር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሁሉ ለማ​ቅ​ረብ፥


አራቱ ሺህም በረ​ኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለም​ስ​ጋና በተ​ሠ​ሩት በዜማ ዕቃ​ዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መክ​ፈቻ የሚ​ይዙ፥ ጥዋት ጥዋ​ትም ደጆ​ቹን የሚ​ከ​ፍቱ እነ​ርሱ ነበ​ሩና።


ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች የነ​በሩ መዘ​ም​ራን በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራ​ቸ​ውም ሌሊ​ትና ቀን ነበረ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።