አለቃው ኤኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ ኢያአስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።
1 ዜና መዋዕል 23:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰሜኢ ልጆች ኤኢት፥ ዚዛ፥ ኢያአስ፥ በሪዓ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤ እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሜኢ ልጆች ኢኢት፥ ዚዛ፥ የዑስ፥ በሪዓ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሺምዒም በዕድሜአቸው ተራ ያሐት፥ ዚዛ፥ ይዑሽና በሪያ ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ያሖት የመጀመሪያው፥ ዚዛ ሁለተኛው ነበሩ፤ ይዑሽና በሪያ ብዙ ልጆች ስላልነበሩአቸው እንደ አንድ ጐሣ ይቈጠሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሜኢ ልጆች ኢኢት፥ ዚዛ፥ የዑስ፥ በሪዓ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ። |
አለቃው ኤኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ ኢያአስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።