1 ዜና መዋዕል 21:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርናም ዘወር ብሎ ንጉሡ ዳዊትን፥ ከእርሱም ጋር ተሸሽገው የነበሩ አራቱን ብላቴኖቹን አየ። ኦርናም ስንዴ ያበራይ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለ ዘወር ሲል መልአኩን አየ፤ ዐብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆቹም ተሸሸጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦርናም ዘወር ብሎ መልአኩን አየ፥ ከእርሱም ጋር የነበሩ አራቱ ልጆች ተሸሸጉ፤ ኦርናም ስንዴ ያበራይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም አውድማ ላይ ራሱ ኦርናና አራት ወንዶች ልጆቹ ስንዴ ይወቁ ነበር፤ መልአኩንም ባዩ ጊዜ ልጆቹ ሮጠው ተደበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርናም ዘወር ብሎ መልአኩን አየ፤ እርሱም ጋር የነበሩ አራቱ ልጆች ተሸሸጉ፤ ኦርናም ስንዴ ያበራይ ነበር። |
የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በኤፍራታ ባለችው ለኤዝሪ አባት ለኢዮአስ በነበረችው ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለማሸሽ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር።