የእግዚአብሔርም መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
1 ዜና መዋዕል 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በእግዚአብሔር ስም እንደ ተናገረው እንደ ጋድ ነገር ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትም ጋድ በእግዚአብሔር ስም በነገረው ቃል ታዝዞ ለመፈጸም ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በጌታ ስም እንደ ተናገረው እንደ ጋድ ቃል ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመፈጸም ጋድ እንደ ነገረው ለማድረግ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በእግዚአብሔር ስም እንደ ተናገረው እንደ ጋድ ነገር ወጣ። |
የእግዚአብሔርም መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
ኦርናም ዘወር ብሎ ንጉሡ ዳዊትን፥ ከእርሱም ጋር ተሸሽገው የነበሩ አራቱን ብላቴኖቹን አየ። ኦርናም ስንዴ ያበራይ ነበር።
እርሱም እየፈራና እየተንቀጠቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እንዳደርግ ትሻለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ይነግሩሃል” አለው።