አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ በጆሮው ገልጠሃልና ስለዚህ አገልጋይህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ።
1 ዜና መዋዕል 17:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም፥ አቤቱ፥ አንተ አምላክ ነህ፤ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላክ ነህ፤ ይህንም መልካም ነገር ለማድረግ ለባሪያህ ተስፋ ሰጥተኸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም፥ አቤቱ፥ አንተ አምላክ ነህ፥ ይህንም መልካም ነገር ለባርያህ ተናግረሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ አምላክ ነህ፤ ይህንንም አስደናቂ የተስፋ ቃል ለእኔ ሰጥተኸኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ አቤቱ! አንተ አምላክ ነህ፥ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል። |
አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ በጆሮው ገልጠሃልና ስለዚህ አገልጋይህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ።
አሁንም በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የአገልጋይህን ቤት ትባርክ ዘንድ ጀምረሃል፤ አንተም አቤቱ፥ ባርከኸዋል፤ ለዘለዓለምም ቡሩክ ይሆናል።”
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።