1 ዜና መዋዕል 16:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤልም ልጆች ይነግራቸው ዘንድ አገልጋዩ ሙሴን እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ለእስራኤልም ባዘዘው በጌታ ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለጌታ ያቀርባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረገው እግዚአብሔር ለእስራኤል በሰጠው ሕግ መሠረት፥ ዘወትር ጠዋትና ማታ በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲያቃጥሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም ባዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ። |
እስከ ሠርክም ድረስ ትንቢት ይናገሩ ነበር፤ ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስና የሚያደምጥም አልነበረም። ከዚህም በኋላ መሥዋዕት በሚያርግበት ጊዜ ኤልያስ ነቢያተ ሐሰትን፥ “እንግዲህስ ወዲያ በቃችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥዋዕቴን እሠዋለሁ” አላቸው።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።
በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በበዓላትም ለሚቀርበው ለሚቃጠለው መሥዋዕት ንጉሡ ከገንዘቡ የሚከፍለውን ወሰነ።
በሀገሩም ካሉት አሕዛብ ፈርተው ነበርና መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት፤ በጥዋትና በማታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡበት።
የስንዴውንም መሥዋዕት አቀረበ፤ ከእርሱም እፍኝ ሙሉ ወስዶ በጥዋት ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ በመሠዊያው ላይ ጨመረው።
“ወደ ቤቴል ገብታችሁ ኀጢአትን ሠራችሁ፤ በጌልገላም ኀጢአትን አበዛችሁ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን አቀረባችሁ፤