1 ዜና መዋዕል 16:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡ ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣ “አሜን፤ እግዚአብሔር ይመስገን” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ።” ሕዝቡም ሁሉ “አሜን” አሉ፤ ጌታንም አመሰገኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡ ሁሉ “አሜን” አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዘላለም እስከ ዘላለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ። |
“እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፥ በባሪያው በሙሴ ቃል ከተናገረው ከመልካም ቃል ሁሉ ያጐደለው አንድም ቃል የለም።
ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፤ በግንባራቸውም ወደ ምድር ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ፤ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ፥ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ትንቢት ይፈጽም።
አንተ በመንፈስ ብታመሰግን፥ ያ የቆመው ያልተማረው በአንተ ምስጋና ላይ እንዴት አሜን ይላል? የምትናገረውንና የምትጸልየውን አያውቅምና።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።