1 ዜና መዋዕል 16:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኀይልና ደስታም በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ ብርታትና ደስታም በማደሪያው ስፍራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤ መቅደሱንም ኀይልና ደስታ እንዲሞላበት አድርጎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኀይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው። |
እርሱም፥ “ሂዱ፤ የሰባውንም ብሉ፤ ጣፋጩንም ጠጡ፤ ለእነዚያም ምንም ለሌላቸው እድል ፈንታቸውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ እግዚአብሔርም ኀይላችን ነውና አትዘኑ” አላቸው።
ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ አምሳያ አየሁ፤ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት አምሳያ አየሁ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ።
አባት ሆይ፥ የሰጠኸኝ እነዚህ እኔ ባለሁበት አብረውኝ ይኖሩ ዘንድና የሰጠኸኝን ክብሬን ያዩ ዘንድ እወድዳለሁ፤ ዓለም ሳይፈጠር ወድደኸኛልና።