La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊ​ትም በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ሩ​አት፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕትም በጌታ ፊት አቀረቡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የቃል ኪዳኑንም ታቦት ወስደው ዳዊት ባዘጋጀው ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ ከዚያም በኋላ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኅብረት መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 16:1
14 Referencias Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደ፤ በጽ​ዮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደ​ረገ።


ንጉ​ሡም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ሠዉ።


ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።


“እና​ንተ የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ናችሁ፤ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላት ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እና​ን​ተና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​ደሱ።


ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ በፈ​ጸመ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ሕዝ​ቡን ባረከ።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


ዳዊት ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም አወ​ጣት። ለእ​ርሷ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ድን​ኳን አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላት ነበ​ርና።


ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ያቀ​ር​ባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀር​ባ​ውም ድረስ የተ​ቈ​ረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥