La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሌዋ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ መዘ​ም​ራ​ኑም፥ የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም አለቃ ኮኖ​ን​ያስ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብ​ሰው ነበር፤ ዳዊ​ትም የከ​በረ ልብስ ለብሶ ነበረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ መዘምራኑና የመዘምራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትን ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊትም፥ ታቦቱንም የተሸከሙ ሌዋውያን ሁሉ፥ መዘምራኑም፥ የመዘምራኑም አለቃ ከናንያ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብሰው ነበር፤ ዳዊትም ኤፉድ ያለበት በፍታ ለብሶ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ከጥሩ በፍታ የተሠራ መጐናጸፊያና ኤፉድ ለብሶ ነበር፤ እንዲሁም መዘምራኑ በሙሉ፥ የመዘምራኑ መሪ ከናንያና የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሌዋውያን ከጥሩ በፍታ የተሠራ ልብስ ለብሰው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም፥ ታቦቱንም የተሸከሙ ሌዋውያን ሁሉ፥ መዘምራኑም፥ የመዘምራኑም አለቃ ከናንያ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብሰው ነበር፤ ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ነበረው።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 15:27
5 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር።


እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


ዳዊ​ትም ታቦቷ በም​ታ​ር​ፍ​በት ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቆ​ማ​ቸው የመ​ዘ​ም​ራን አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው።


መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።