ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ከፈጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያንጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት ንጉሡ ሰሎሞን በጽዮን ሰበሰባቸው።
1 ዜና መዋዕል 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድ-ኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት፥ የእስራኤል ሕዝብ መሪዎችና የጦር አዛዦች የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዱ፤ ከፍ ያለ የደስታ ሥነ ሥርዓትም አደረጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊት፥ የእስራኤል ሽማግሌዎችና ሻለቆች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ። |
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤተ መንግሥት ሠርቶ ከፈጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያንጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች የአባቶቻቸውን ቤቶች መሳፍንት ንጉሡ ሰሎሞን በጽዮን ሰበሰባቸው።
ዳዊት ግን የእግዚአብሔርን ታቦት ከቂርያትይዓሪም አወጣት። ለእርሷ በኢየሩሳሌም ድንኳን አዘጋጅቶላት ነበርና።
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
የእስራኤልም ልጆች ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ የቀሩትም የምርኮኞች ልጆች የዚህን የእግዚአብሔርን ቤት ቅዳሴ በደስታ አደረጉ።
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
ከእናንተም ጥበበኞችና ዐዋቂዎች፥ አስተዋዮችም የሆኑትን ሰዎች ወሰድሁ፤ በእናንተም ላይ አለቆች፥ የሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የአምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም፥ ለፈራጆቻችሁም ጻፎች አድርጌ ሰየምኋቸው።
ነገር ግን አንተ፥ ወንድና ሴት ልጅህም፥ ወንድና ሴት አገልጋይህም፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው መጻተኛ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ብሉት፤ እጅህንም በምትዘረጋበት ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ።
በዚያም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብሉ፤ እጃችሁንም በምትዘረጉበት፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በባረካችሁ ነገር ሁሉ፥ እናንተና ቤተሰባችሁ ደስ ይበላችሁ።
አንተ፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመካከልህም ያሉ መጻተኛና ድሃ-አደግ፥ መበለትም አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
አምላክህ እግዚአብሔር ለራሱ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በፍሬህ ሁሉ፥ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና። አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃልና።
ግዙራንስ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናገለግለውና የምናመልከው እኛ ነን፤ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስ እንመካለን እንጂ በሥጋችን የምንመካ አይደለም።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን እግዚአብሔርን ንቃችሁ፦ ‘እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ” አላቸው።
ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ብላቴኖች፥ “ብንያማውያን ሆይ! እንግዲህ ስሙ በእውነት የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ መቶ አለቆችና ሻለቆች ያደርጋችኋልን?
ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች የአምሳ አለቆችም ያደርጋቸዋል፤ እርሻውንም የሚያርሱ፥ እህሉንም የሚያጭዱ፥ ፍሬውንም የሚለቅሙ፥ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ያደርጋቸዋል።