ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘካርያስ፥ አዝኤል፥ ሰሚራሞት፥ ኢያሔል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያ፥ በናያስ በመሰንቆ በልዑል ቃል ያዜሙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘካርያስ፣ ዓዝኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ መዕሤያና በናያስ ደግሞ በአላሞት ቅኝት መሰንቆ ይገርፉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘካርያስ፥ ዓዝዔል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያ፥ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘካርያስ፥ ዓዝዔል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያና በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ነበር። |
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ተራ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ አዝኤልን፥ ስሜራሞትን፥ ኢያሄልን፥ ኡኒን፥ ኤልያብን፥ በናእያን፥ መዕሤያን፥ መታትያን፥ ኤልፋይን፥ ሜቄድያን፥ በረኞችንም አብዲዶምን፥ ኢያኤልንና ዖዝያስን አቆሙ።