ከሰዎችም ሁሉ ይልቅ ብልህ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከአውናንና ከከልቀድ፥ ከደራልም ይልቅ ጥበበኛ ነበረ። በዙሪያውም ባሉ አሕዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።
1 ዜና መዋዕል 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዘምራንም ኤማንና አሳፍ ኤታንም በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዘምራኑ ኤማን፣ አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መዘምራንም የነበሩት ኤማንና አሳፍ ኤታምንም የናሱን ጸናጽል ድምፅ ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መዘምራንም ኤማን አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር። |
ከሰዎችም ሁሉ ይልቅ ብልህ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከአውናንና ከከልቀድ፥ ከደራልም ይልቅ ጥበበኛ ነበረ። በዙሪያውም ባሉ አሕዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
ዳዊትም በዜማ ዕቃ፥ በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን “ወንድሞቻችሁን ሹሙ” ብሎ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ተራ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ አዝኤልን፥ ስሜራሞትን፥ ኢያሄልን፥ ኡኒን፥ ኤልያብን፥ በናእያን፥ መዕሤያን፥ መታትያን፥ ኤልፋይን፥ ሜቄድያን፥ በረኞችንም አብዲዶምን፥ ኢያኤልንና ዖዝያስን አቆሙ።
ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታም ልጆች ግን በረኞች ነበሩ።
አለቃውም አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዘካርያስ፥ ኢያሔል፥ ሰሜራሞት፥ ይሔኤል፥ ማታትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ አብዲዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና፥ አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶትምም ልጆች በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም የሚዘምሩ ሰዎችን ለማገልገል ለዩ፤ በየአገልግሎታቸውም ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር።
ሌዋውያንም፥ ከቀዓት ልጆችና ከቆሬ ልጆች የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ።
ካህናቱም በየሥርዐታቸው ሌዋውያኑም ደግሞ፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር።