ዳዊትም አምላኩ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ።
1 ዜና መዋዕል 14:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ዝና በየሀገሩ ሁሉ ወጣ፤ መፈራቱንም እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊትም ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ መፈራቱንም ጌታ በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ አደረገው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊትም ዝና በየቦታው ተሠራጨ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተፈራ እንዲሆን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ዝና በየአገሩ ሁሉ ወጣ፤ መፈራቱንም እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ አደረገው። |
ዳዊትም አምላኩ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ።
በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆች ስም ለአንተ ስምን አደረግሁ።
በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ እንደ ተናገራችሁ፥ ማስፈራታችሁን፥ ማስደንገጣችሁንም በምትረግጡአት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል።
ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ስምህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።
መልሰውም ኢያሱን፥ “እኛ ባሪያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ ይሰጣችሁ ዘንድ፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ ያጠፋ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፤ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፤ ይህንም ነገር አድርገናል፤