ዳዊትም ከላይኛው መጋደያ መጣ፤ በዚያም መታቸውና፥ “ውኃ እንደሚያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን ፍልስጥኤማውያንን በፊቴ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “የላይኛው መጋደያ” ተብሎ ተጠራ።
1 ዜና መዋዕል 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲን ወጣ፤ በዚያም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታቸው። ዳዊትም፥ “ውኃ እንዲያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲን ብለው ጠሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤ በዚያም ድል አደረጋቸው። ዳዊትም፣ “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ ሁሉ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በእጄ አፈራረሳቸው” አለ፤ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ በኣል-ፐራሲምም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት ድል ነሣቸው። ዳዊትም፦ “ግድቡን አፍርሶ እንደሚወጣ ጎርፍ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣል-ፐራሲም ብለው ጠሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዳዊት ባዓልፈራጺም ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ ድል ካደረጋቸው በኋላ “የጠላትን ሠራዊት እንደ ጐርፍ ጥሼ እንዳልፍ እግዚአብሔር ረዳኝ” አለ፤ ከዚያም በኋላ ያ ስፍራ “ባዓልፈራጺም” ተብሎ ተጠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ በኣልፐራሲምም ወጡ፤ በዚያም ዳዊት መታቸው። ዳዊትም “ውሃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው፤” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም “በኣልፐራሲም” ብለው ጠሩት። |
ዳዊትም ከላይኛው መጋደያ መጣ፤ በዚያም መታቸውና፥ “ውኃ እንደሚያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን ፍልስጥኤማውያንን በፊቴ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “የላይኛው መጋደያ” ተብሎ ተጠራ።
ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው።
ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን፥ ፈረሰኞችንም፥ የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመጡትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም።
እግዚአብሔርም በኃጥኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፤ በገባዖን ሸለቆም ይኖራል፤ ሥራውን ማለት መራራ ሥራውን በቍጣ ይሠራል፤ ቍጣውም ድንቅን ያደርጋል፤ መርዙም ልዩ ነው።