ከዚያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን ውጣ” አለው።
1 ዜና መዋዕል 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት፣ “በፍልስጥኤማውያን ላይ ወጥቼ ልምታቸውን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፦ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። ጌታም፦ “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “በፍልስጥኤማውያን ላይ ጦርነት ልክፈትን? በእነርሱስ ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ፥ አደጋ ጣልባቸው! እኔም ድልን አጐናጽፍሃለሁ!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ፤” አለው። |
ከዚያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን ውጣ” አለው።
ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥ “ፍልስጥኤማውያንን በርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው።
ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ የሚያህሉትን ሰዎች ሰበሰበ፤ የእስራኤል ንጉሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም፥ “እግዚአብሔር በንጉሥ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ” አሉት።
ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲን ወጣ፤ በዚያም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታቸው። ዳዊትም፥ “ውኃ እንዲያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲን ብለው ጠሩት።
ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “አትውጣ፥ በኋላቸውም አትከተላቸው፤ ነገር ግን ከኋላቸው ዙረህ ቅረባቸው።
ዳዊትም፥ “የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፥ “ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮኞቹን ታድናለህና ፍለጋቸውን ተከተል” ብሎ መለሰለት።