በጭፍራውም ውስጥ ዳዊትን ለመርዳት የወጡ የተዘጋጁ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ ደካማ አልነበረም።
1 ዜና መዋዕል 12:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጭፍራውም ውስጥ የሚወጡ፥ ለሰልፍም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአሴር ሰዎች ልምድ ያላቸውና ለጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች አርባ ሺሕ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽኑ የሠለጠኑ ተዋጊዎች፥ ለውጊያም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጭፍራውም ውስጥ የሚወጡ፥ ለሰልፍም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ። |
በጭፍራውም ውስጥ ዳዊትን ለመርዳት የወጡ የተዘጋጁ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ ደካማ አልነበረም።
በዮርዳኖስም ማዶ ካሉ ከሮቤልና ከጋድ ሰዎች ከምናሴም ነገድ እኩሌታ የጦር መሣሪያንም ሁሉ ይዘው የመጡ መቶ ሃያ ሺህ ነበሩ።
እንደ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፤ እንደ ጦረኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፤ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።