1 ዜና መዋዕል 12:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋር ጽኑዕ ኀያል ጐልማሳ ሳዶቅ ነበረ፤ ከአባቱም ቤት ሃያ ሁለት አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ሳዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ጋር ጽኑዕ ኃያል ጎልማሳ ሳዶቅ ነበረ፥ ከአባቱም ቤት ሀያ ሁለት የጦር አዛዦች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ጽኑዕ፥ ኀያል ጐልማሳ ሳዶቅ ነበረ፤ ከአባቱም ቤት ሃያ ሁለት አለቆች ነበሩ። |
ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነቢዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳዊትም ኀያላን አዶንያስን አልተከተሉም ነበር።
ንጉሡም በእርሱ ፋንታ የዮዳሄን ልጅ በንያስን የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመ፤ መንግሥቱም በኢየሩሳሌም ጸናች። በአብያታርም ፋንታ ካህኑን ሳዶቅን ሾመ።
በቀበሳኤል የነበረው፥ ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ እንደ አንበሳ ኀያላን የነበሩትን ሁለት የሞዓብ ሰዎች ገደለ፤ በአመዳይም ወራት ወርዶ በጕድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።
ዳዊትም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፥ ሌዋውያንንም፥ ኡርኤልን፥ ዓሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሰማያን፥ ኤሊኤልን፥ አሚናዳብንም ጠርቶ፦
በሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሽህ ጭፍራ ነበረ።
“ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዐት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።