1 ዜና መዋዕል 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነበረ ጊዜ የተሻገሩት እነዚህ ናቸው፤ በሸለቆውም ውስጥ በምሥራቅና በምዕራብ በኩል የተቀመጡትን ሁሉ አባረሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ፣ ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነበረ ጊዜ የተሻገሩት እነዚህ ናቸው፤ በሸለቆውም ውስጥ በምሥራቅና በምዕራብ በኩል የተቀመጡትን ሁሉ አባረሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም የጋድ ነገድ አባሎች በአንድ ወቅት የዓመቱ የመጀመሪያ ወር እንደ ገባ፥ የዮርዳኖስም ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ ወንዙን ተሻገሩ፤ ከወንዙ በሰተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ በሸለቆዎቹ ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አባረሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነበረ ጊዜ የተሻገሩት እነዚህ ናቸው፤ በሸለቆውም ውስጥ በምሥራቅና በምዕራብ በኩል የተቀመጡትን ሁሉ አባረሩ። |
እግሮችህ ሮጠው ይደክማሉ፤ ፈረሶችን ለምን ታስጌጣለህ? በሰላምም ምድር ላይ ለምን ትታመናለህ? በዮርዳኖስስ ጩኸት ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?”
እንደ ክረምትና እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እስከ ወሰኑ ሞልቶ ነበርና የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ በገቡ ጊዜ፥ ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃዉ ዳር ሲጠልቁ፥
የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜ፥ በእግራቸውም የብስ በረገጡ ጊዜ፥ የዮርዳኖስ ውኃ ተወርውሮ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ ቀድሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።