1 ዜና መዋዕል 1:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአክቦር ልጅ በኣልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ የባራድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፌጎር ነበረ፤ ሚስቱም የሚዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኣልሐናን ሲሞት ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የእርሱም ከተማ ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የማጥሬድ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች፤ ሃዳድም ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓልሐናን በሞተ ጊዜ የፋዑ ተወላጅ የነበረው ሀዳድ ነገሠ፤ ሚስቱም መሄጣብኤል የምትባል የዛሀብ የልጅ ልጅ የማናሬድ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኣልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፋንታ ሐዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች፤ ሃዳድም ሞተ። |
የአክቦር ልጅ በአልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስቱም የሜዛአብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ምኤጠብኤል ትባላለች።