መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
1 ዜና መዋዕል 1:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማውም ስም ዲናባ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማይቱም ስም ዲንሃባ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤል ምንም ንጉሥ ባልነገሠበት ዘመን የሚከተሉት ነገሥታት በኤዶም ምድር በየተራ ነግሠዋል፦ የከተማው ስም ዲንሃባ ይባል የነበረው የበዖር ልጅ ቤላዕ ነገሠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማይቱም ስም ዲንሃባ ነበረ። |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤