ሶፎንያስ 2:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሞዓብን ስድብ፣ የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ፤ በሕዝቤም ላይ አላግጠዋል፥ በድንበራቸውም ላይ ኮርተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞአብን ሕዝብ ፌዝና የአሞንን ሕዝብ ስድብ ሰምቼአለሁ፤ እነርሱም እንዴት አድርገው እንዳፌዙባቸውና ርስታቸውንም ለመውሰድ እንደ ዛቱባቸው ዐውቄአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ። |
ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤ የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤ በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች። የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣ በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠሁትን ርስት የሚይዙትን ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ፤
ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።
ስለ አሞናውያን፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስራኤል ወንዶች ልጆች አልወለደምን? ወራሾችስ የሉትምን? ታዲያ፣ ሚልኮም ጋድን ለምን ወረሰ? የርሱ ሰዎች ለምን በከተሞቿ ይኖራሉ?
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሰይፍ! ሰይፍ! ሊገድል የተመዘዘ፣ ሊያጠፋ የተጠረገ፣ እንደ መብረቅ ሊያብረቀርቅ የተወለወለ፤
ከዚያም ስለ እስራኤል ተራሮች፣ “ጠፍ ሆነዋል፤ ቦጫጭቀን እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ በንቀት የተናገርኸውን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁ በዚያ ጊዜ ታውቃለህ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ድንበሩን ለማስፋት፣ የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀድዷልና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የሞዓብ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ የኤዶምን ንጉሥ ዐጥንት፣ ዐመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሏልና፤
ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነሆ፤ ዛሬ የግብጽን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው፤ ከዚህም የተነሣ የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተባለ።