ሮሜ 5:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽናትም የተፈተነ ባሕርይን ያስገኝልናል፥ የተፈተነ ባሕርይም ተስፋን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከትዕግሥትም በፈተና መጽናት፥ ከመጽናትም ተስፋ ይገኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕግሥትም መከራ ነው፤ በመከራም ተስፋ ይገናል። |
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።