እንደ አባቶቻችሁም ዐንገተ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ እርሱ ለዘላለም ወደ ቀደሰውም መቅደስ ኑ። አስፈሪ ቍጣው ከእናንተ እንዲመለስም፣ እግዚአብሔር አምላካችሁን አገልግሉ።
መዝሙር 75:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትምክህተኞችን፦ “አትኩሩ፥ ክፉዎችንም፦ ቀንዳችሁን አታንሡ፥” አልኋቸው አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ላይ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ ወይም በትዕቢት አትናገር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥ ሕልምን አለሙ፥ ያገኙት ግን የለም፤ ሰው ሁሉ ለእጁ ባለጠግነት ነው። |
እንደ አባቶቻችሁም ዐንገተ ደንዳኖች አትሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ እርሱ ለዘላለም ወደ ቀደሰውም መቅደስ ኑ። አስፈሪ ቍጣው ከእናንተ እንዲመለስም፣ እግዚአብሔር አምላካችሁን አገልግሉ።
የቱን ያህል ዐመፀኞችና ዐንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ ዐውቃለሁና። እኔ በሕይወት ከእናንተ ጋራ እያለሁ በእግዚአብሔር ላይ ካመፃችሁ፣ ከሞትሁ በኋላማ የቱን ያህል ልታምፁ!