መዝሙር 63:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐመፃን ፈለጓት፥ ሲፈትኑም ሲጀምሩም አለቁ፤ ሰው በጥልቅ ልብ ውስጥ ይገባል፥ |
እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”
የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣ ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤ በጌታ ፊት፣ ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤ በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለ ወደቁት፣ ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።