መዝሙር 31:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ በደነገጥሁ ጊዜ፣ “ከዐይንህ ፊት ተወግጃለሁ” አልሁ፤ አንተ ግን ወደ አንተ ስጮኽ፣ የልመናዬን ቃል ሰማህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ ጌታ ይመስገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከድንጋጤዬ የተነሣ ከፊትህ ያራቅኸኝ መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን ርዳታህን ፈልጌ ለምሕረት ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ሰማህ። |
እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ዐጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እንዲህም ይላሉ፤ ‘ዐጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ የለንም፤ ተቈርጠናል።’
ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋራ አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።
ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፣ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከብበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፣
ዳዊት ግን በልቡ፣ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፣ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ ዐሰበ።