እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
ከድንኳን በሚወጣበት ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር። የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለጌታ አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለጌታ አምጡ።
እናንተ የሰማይ መላእክት ሁሉ፥ ክብርና ኀይል የእግዚአብሔር ነው በሉ።
አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ የጠላቶቼ መዘባበቻ አላደረግኸኝምና አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኀይልና ብርታትን ይሰጣል። እግዚአብሔር ይባረክ!
እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣ በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።
ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ ፈጽሞም ይደመሰሳል።