ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈስሳል።
ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፥ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
ከዚህ በኋላ ትእዛዝ ይሰጣል፤ የተጋገረውም በረዶ ይቀልጣል፤ ነፋስን ያነፍሳል፤ ውሃም ይፈስሳል።
የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።
ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ባለች ጊዜ፣ ከሙቀት የተነሣ በልብስህ ውስጥ የምትዝለፈለፍ ሆይ፤
ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።
ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።
እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።
የምሥራቁን ነፋስ ከሰማይ አስነሣ፤ የደቡብንም ነፋስ በኀይሉ አመጣ።