ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤ ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።
አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፥ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፥
ዐመዳዩን እንደ ባዘቶ ያነጥፈዋል፤ ውርጩንም እንደ ዐመድ ይበትነዋል።
በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል።
“ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃልን? የዐመዳዩንስ ማከማቻ አይተሃልን?
በረዶ ከማን ማሕፀን ይወጣል? የሰማዩንስ ዐመዳይ ማን ይወልዳል?
እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣
ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣